በመጽሔት ከሸኘን በኋላ! በእግራችን እየተራመድን ልክ ትምሕርት ሚንስቴር ሕንፃጋ ሥንደርሥ “ሳምኬት” ቆም እንድንል ካዘዘችኝ በኋላ አይኖTን አራት _ ኪሉ አደባባይ መሃል ላይ ለአርበኞች መታሠቢያነት ወደተሠራው ሃውልት ላይ ልካ
“እዚህ ሃውልት ጫፍ ላይ ያለውን ሠዓት አየኸው" ጥያቄ ነው ከእርሷ ለእኔ ብዙ ጊዜ ለእንደዚህ አይነት ነገሮች ልዩ
ትኩረት ትሠጣለች ይኸውም የትምህርቷ ዝንባሌ የሚፈጥረው ልዩ ስሜት መስሎ ሥለሚሰማኝ ለነገሮቹ ያለኝ ምልከታ የተለየ ቢሆንም እርሷ የምትሠጠውን ትንተና (Analysis) ለመስማት ሥል ልዩ ትኩረት አድርጌ ሕሊናዬን ወደ ነገሮቹ እሠበስባለሁ ዛሬም እንደዚያው መስሎኝ… ሃውልቱ ጫፍ ላይ የሚገኘውን ሠዓት ለግማሽ ደቂቃ ያህል ካስተዋልኩ በኋላ
“አዎን አየሁት ግን ሰባት ሰዓት ላይ ብቻ የቆመ ይመስላል “ትክክል” ፈጠን ብላ ልክ ነህ ሠዓቱ ሃያ አራቱም ሰዓት ላይ ብታየው ሰባት ሰዓት ላይ እንደቆመ ነው፡፡
አልፎ ሂያጅ አላፊ አግዳሚዎች የሁለታችን ሰዓቱ ላይ ማፍጠጥ አስገርሟቸው ጤነኛ ናቸው? በሚል ሁኔታ ከገረመሙን በኋላ አይኖቻቸውን ወደሀውልቱ መለስ እያደረጉ የፌዝ ሳቅ አሳይተውን መንገዳቸውን ይቀጥላሉ፡ ምናልባትም “ሲያሳዝኑ" እያሉ እኔም የሰዓቱ ከሰባት በላይም ሆነ በታች አለመንቀሳቀሱ የተቃወሙጊዜ ኢትዮጵያን በወረረ“ጣሊያን አርበኞች በዱር በገደል የነበሩት በድል አድራጊነት ወደ መሀል ከተማ የገቡበትና የተሰባሰቡበት ሰዓት ሰባት ሰዓት መሆኑን” የማውቀውን በመጠኑ መለስኩ፡፡
እርሷም አይኖቼን በአይኖቿ ለተወሰኑ ቅዕበታት በትኩረት አይታ የቀኝ እጇን መዳፍ በግራ እጆቼ መዳፍ ጡስጥ አቆላልፋ የመገናኛን አቅጣጫ የፊታችንን መንገድ አየር እየሰነጠቅን “ልክ ነህ ለእኔ ግን ከዚያም በላይ ትርጉም ይሰጠኛል”“ከዚያ በላይ የሆነ አንቺ ምን አይነት ትርጉም አገኘሽበት መልሼ እኔ ጠየቅኩኝ
“ምንም እንኳን ሰዓቱ ሰባት ላይ እንዲቆም መደረጉ አርበኞቹ ሀገራችንን አናስደፍርም1 የሚያገኘንም ሁሉ አይገድለን
ፈፅሞ ብለው እንቢታቸው!አሻፈረኝ ባይነታቸው በድል መሽገው ከየነበሩበት ሥፍራ ወደ መሀል ከተማ ተመልሰው
የተሰባሰቡበት መታሰቢያ ቢሆንም የዚህ ሰዓት “ሰባት” ላይ መቆም ግን ከዚያ በኋላ በመጡት ትውልዶች ላይ ትዝብትና ሥላቅ ይመስለኛል"
“ምን አይነት ትዝብት ምንስ አይነት ስላቅ"
“ምናልባት የምነግርህ ነገር የግሌ አመለካከት ሊሆን ይችላል ለሌላ ሰውም ትምህርት ላይሰጥ ይችላል ቢሆንም ግን ጠያቄዬ አንተ ነህና ነግርሃለሁ"
“እባክሽን”
“ለእኔ ሀውልቱ ላይ ያለው ሰዓት እንደቆመ መቅረቱ በሀገራችን ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያዊ ትርጉም ያለው ሥራ አለመሰራቱን እና እንዲሁም ደግሞ ተሰርቶ የነበረው የደጋጎቹ ምልክት ጠፍቶ መቅረቱን የሚናገር የሥላቅና የትዝብት ምልክት ነው ሰነፎች, የሚወቅስ"
ከዚህ በኋላ በሁለታችን መሀል የነበረው ወግ ምንም አይነት ድምጽ የሌለው ስሜታዊ መግባባት ብቻ ነበር፡፡
0 Comments
Post a Comment